ጌቴሴማኒ
- Redeatu G. Kassa
- Mar 30, 2015
- 1 min read
ጌቴሴማኒ የአትክልት ምድር፣ እማኝ አድርጌ ልጥራሽ ምስክር፣ አድምጠሻልና የሰውን ልጅ ጽዋ ጣር። የአባቱን ፊት ሲሻ፣ ሊሞላለት የፍቃዱን ድርሻ፣ ሲጨክን ሊሸከም መስቀሉን፣ ታዝበሻልና መራራ ትግሉን። ጌቴሴማኒ ንገሪኝ የሰዓቲቱን ጭንቅ፣ የሰው ልጅ ኃጢያት ሆኖ ሊደቅቅ፣ የመስቀሉን ጽዋ ሊጨልጥ ሲማቅቅ። ንገሪኝ እሲቲ ጌቴሴማኒ የአትክልት ስፍራ፣ የመታዘዙን ሚስጢር በፈቃዱ የመግባቱን መላ፣ የኃጢያትን ጽዋ ሲጨልጥ መከራ፣ ስራውን ሊፈጽም የሕይወቱን እንጀራ፣ መንፈስ ተዘጋጅታ ስጋ በደከመበት ስፍራ። የደሙን ነጠብጣብ ላብ ጠጥተሻልና፣ ታዝበሻልና የመራሩን ጽዋ ፈተና፣ የቆረጠበቱን ሊያቀና ጎልጎታ፣ ካራው ወደ ሚያርፍበቱ ቦታ። በሰው ቦታ ገብቶ ለመስቀል ሞት ታዞ ሊቀጣ፣ ልጆችን ሊወልድ ሲያምጥ የጽድቅን ፍሬ ሊያወጣ፣ ወልድ ሲጨክን በኃጢያት ፍርድ ሊመታ፣ ደሙ ካፈርሽ ሲዋሃድ ታዝበሻል ጌቴሴማኒ የአትክልት ቦታ። ጌቴሴማኒ የአትክልት ምድር፣ እማኝ አድርጌ ልጥራሽ ምስክር፣ አድምጠሻልና የሰውን ልጅ ጽዋ ጣር።
Recent Posts
See All“ተስፋን ቃል የሰጠዉ የታመነ ነዉና እንዳይነቃነቅ የተስፋችንን ምስክርነት እንጠብቅ። (ዕብ 10፡ 23) ተስፋ ሰው በሕይወቱ እንደሚሆን በእርግጠኝነት የሚጠብቀው ነገር ነው። እያንዳንዱ ሰዉ ተስፋ የሚያደርገዉ...
ባለንበት ጊዜ በተለይም በ COVID 19 ወረርሽኝ የተነሳ በአብዛኛው ቤት ውስጥ ተከተን ባለንበት በዚህ ወቅት፤ የተለያየ ድምጽ፣ አስተሳሰብ፣ ጩኸት፣ አመለካከት እና ፕሮፓጋንዳ የምንሰማበት አጋጣሚ ሰፊ ነው። በተለይም...
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተለይም በምእራቡ አለምና በሃገራችን በኢትዮጲያ በተወሰነ መልኩ በትምህርት ቤቶች፣ በአንዳንድ ቢሮዎች፣ በቤትና በአፓርትመንት መስኮቶች ላይ በወረቀት የተቀለመ ህብረቀለማትን አዋህዶ የያዘ...
Comentários