top of page

አቤንኤዘር!

“ሳሙኤልም አንድ ድንጋይ ወስዶ በምጽጳና በሼን መካከል አኖረው ስሙንም። እስከ

አሁን ድረስ እግዚአብሔር ረድቶናል ሲል አቤንኤዘር ብሎ ጠራው።” (1 ሳሙ 7፡12)

እንኳን ለቤተ ክርስቲናችን ሰባተኛ አመት በዓል ጌታ አደረሳችሁ። እንዱም እንኳን

ለ2010 የኢትዮጵያ አዲስ አመት ዋዜማ ጌታ አደረሳችሁ። በ2010 ክረምት ላይ ጥቂት ወንድሞችና

እሕቶች እሁድ እየተገናኙ መጸለይ ጀመሩ። በቤት የጸሎት ሕብረት የተጀመረው አገልግሎት ጌታ

ባርኮት በመጀመሪያ ወደ ሕብረት በመቀጠልም ወደ ቤተ ክርስቲያን ደረጃ አደገ። ቤተ

ክርስቲያናችን September 12 ቀን 2010 በሬቨንስውድ ባብቲስት ክርስቲያን ትምህርት ቤት

በአንድ ክፍል ውስጥ ተጀመረች።

እግዚአብሔር በቤተ ክርስቲናችን እና በሕይወታችን የሰራውን የማዳን ስራ፣ የመታደግ

ስራ እንዘክርና እንመሰክር ዘንድ ይገባናል። ተፈውሰው ለምስጋና እንደጎደሉት ዘጠኙ ለምጻሞች

ሳይሆን ለማመስገን እንደተመለሰው አንዱ እኛም ዛሬ ያሳላፍናቸውን ሳባት የምህረትና የበረከት

አመታት እያሰብን እናመሰግናለን። እግዚአብሔር ውለታውን እንረሳ ዘንድ አይፈልግም።

እግዚአብሔር እስራኤልን ከግብጽ ምድር ሲያወጣው በዘመኑ ሁሉ የእርሱን ማዳን እያሰበ፣

ማዳኑን ለመጪው ትውልድ እየዘከረ የፋሲካን በዓል እንዲያደርግ አዘዘው። ስለዚህም ዛሬም እኛ

መዝሙረኛው ዳዊት እንደዘመረው ነብሳችንን “ነፍሴ ሆይ፥ እግዚአብሔርን ባርኪ፥ ምስጋናውንም

ሁሉ አትርሺ” እያልን የእግዚአብሔርን ውለታ እያሰብንና እየቆጠርን ልናመሰግነው ይገባናል።

(መዝ. 103፡2)

ባሳለፍናቸው ሰባት አመታት በጌታ ቸርነት ብዙ መልካም ነገሮች በመካከላችን ሆነዋል።

የቤተ ክርስቲያንችን መዋቅር ተጠናክሯል፤ አገልግሎቶች በዝተውልናል፤ የቅዱሳን ሕብረት

አድጓል። ብዙ ጌታ የቀባቸው አገልጋዮች በመካከላችን ተገኝተው አስተምረውናል፤ መክረውናል።

ትዝታ የተሞሉ የሕብረት ጊዜዎችን አሳልፈናል። ወገኖች ሲጠመቁ፣ በቅዱስ ጋብቻ ሲጣመሩ፣

ሕጻናት ለጌታ ሲሰጡ፣ ሰዎች ወደ ጌታ ሲመጡ አይተናል። ወንጌሉን ይዘን ወጥተን ማዳኑን

መስክረናል። በጸሎት በፊቱ በመውደቅ ቃትተናል። ከሕጻናቶቻችን አንደበት የምስጋና ዜማ

ሲወጣ፤ ቃሉ ሲነገር ሰምተናል። በዘመኑ ሚዲያ በመጠቀም የወንጌሉን ቃል በቅርብም በሩቅም

ላሉ ሁሉ ለማድረስ ጥረናል። የምንወዳቸው ወገኖች በተለዩንም ጊዜ ጌታ አጽናንቶናል።

ዛሬ ጠንካራ የሆነ የሽማግሌዎች አመራር ቡድን አለን። በብዙ የወንድሞችና የአህቶች

ሕብረት፣ በብዙ የሆድ ፍሬ፣ በብዙ የአገልግሎት ጸጋ ተባርከናል። እግዚአብሔር በቤተሰባዊ

ህብረት፣ የቃሉን ደጅ በመክፈት፣ በክብሩ መገኘትና በመንፈሱ ልእልና ባርኮናል። ከሌሎች ቅዱሳን

ጋር ያለንን ሕብረት በማደስና በማጠንከር ጌታ አዲስ ምዕራፍ ከፍቶልናል። በእርግጥም እስከ

አሁን ድረስ እግዚአብሔር ረድቶናል፣ ደግሞም ይረዳናል። አቤንኤዘር!


Recent Posts
Archive
Search By Tags
Follow Us
  • Facebook Basic Square
  • Twitter Basic Square
  • Google+ Basic Square
spotify-badge-button-listen-wh-BG.png
apple-podcasts-logo.jpg
Google-Podcasts-Badge.jpg
RadioPublicc.png
breaker.png
pocketcasts3.png
Anchor-Podcast-Logo.png

 

5850 N. Elston Avenue 

Chicago, Il 60646

10:00 AM TO 12:00 PM SUNDAY

7:00PM TO 9:00PM FRIDAY

  • Facebook Social Icon
  • Twitter Social Icon
  • Google+ Social Icon
  • YouTube Social  Icon
bottom of page