top of page

እግዚአብሔርን የሚፈራ ሌላ አይፈራም!

ከ2013 በጸጋው ታደለ የሚባል ወንድም በአትላንታ ከተማ ከሚገኘው ሞርሃውስ ኮሌጅ 3.99 በማምጣት በኮምፕተር ሳይንስና በሂሳብ ትምህርት ተመረቀ። ይህን እጅግ በጣም ከፍተኛ ውጤት በማምጣቱም በወቅቱ ለምሩቃኑ ንግግር ያደረጉት ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ የተመራቂውን ስምና ትክለ-ሰውነት ከራሳቸው ጋር በማመሳሰል አመስግነውት ነበር። ወንድም በጸጋውም በእለቱ ከፕሬዝዳንቱ እጅ የክብር ሽልማት ተቀብሏል። የበጸጋው አኩሪ ውጤት በበርካታ የመገናኛ ብዙኋን የተዘገበ ሲሆን በወቅቱ ከቀሩቡለት ጥያቄዎች መካከል “ፕሬዝዳቱን ስታገኝ ፍረሃት አልተሰማህም ወይ” የሚል ነበር። በጸጋው ሲመልስ “እኔ አስቀድሜ በመለዳ ሰማይና ምድርን በፈጠረው ንጉስ ፊት ቀርቤ ስለምወጣ ሌላ ንጉስ አያስፈራኝም” የሚል ነበር።

መጽሐፍ ቅዱስ “የጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሔርን መፍራት ነው ቅዱሱንም ማወቅ ማስተዋል ነው” ይለናል። (ማሳሌ 9፡10) በእርግጥም ማንም ጥበበኛ ነኝ የሚል እግዚአብሔርን የማይፈራ ቢኖር የርሱ ጥበብ ከንቱ ነው። ጥበብ እራሷ ጀመሪዋ እግዚአብሔር ነው። እግዚአብሔርን መፍራት ማለት ለእግዚአብሔር የሚገባውን ክብር መስጠትና ትእዛዙን መጠበቅ ነው። እግዚአብሔር የሚፈራው ከፍቅሩና ከአባትነቱ የተነሳ ነው። የተመሰገነ አባት እንደሚፈራና እንደሚከበር ሁሉ እግዚአብሔር እንዲሁ ሊፈራና ሊከበር ይገባዋል። እግዚአብሔር ህዝቡን “እናንተ ስሜን የምታቃልሉ ካህናት ሆይ፥ ልጅ አባቱን፥ ባሪያም ጌታውን ያከብራል እኔስ አባት ከሆንሁ ክብሬ ወዴት አለ? ጌታስ ከሆንሁ መፈራቴ ወዴት አለ?” በማለት የጠይቃል። እግዚአብሔር ህዝቡ እንደ አባትነቱና ጌትነቱ እንዲያከብረው እና እንዲፈራው ይፈልጋል።

ወገኖቼ፦ በእርግጥም ንጉሱን እግዚአብሔርን የሚፈራ ሌላ ማንንም አይፈራም። መጀመሪያውና መጨረሻው እርሱ ነው። እርሱ የሁሉ የበላይና ገዢ ነው። ሞት ድል የተነሳው በእርሱ ነው። እግዚአብሔርን ከፈራን ሰው አይስፈራንም፤ እግዚአብሔርን ከፈራን ያለንበት ሁኔታ አያስፈራንም። እርሱን ከፈራን ቀና ብለን እንሄዳለን። ምክነያቱም እርሱን ከፈራን እርሱ ከኛ ጋር ይሆናል። እርሱ ከኛ ጋር ከሆነ ማንም ሊቃወመን አይችልም። እርሱን ብቻ ስንፈራ ዳዊት እንደዘመረው “እግዚአብሔር ረዳቴ ነው፥ አልፈራም ሰው ምን ያደርገኛል?” እንላለን። እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰው በእርሱ ጥበቃ ውስጥ ያድራል። ብዙ አስፈሪ ነግሮች በዙሪያው ቢሆኑም እርሱ ግን በእግዚአብሔር ላይ በመታመን ይወጣል፣ ይገባል። የተጣለና ለጠላት አልፎ የሚሰጥ አይሆንም። በእርግጥም በእግዚአብሔር ጥበቃ ውስጥ ተማምኖ ይኖራል። በወቅቱ ነፋስ እየተፍገመገመ ሰላሙ አይወሰድም። ማንኛውንም ጉዳይ የበላይ ወደ ሆነው አምላኩ ያቀርባል ነገር ግን አይታወክም። ምክንያቱም በእርሱ ዘንድ መፍተሔ እንዳለ ያውቃል። አሜን!


Recent Posts
Archive
Search By Tags
Follow Us
  • Facebook Basic Square
  • Twitter Basic Square
  • Google+ Basic Square
bottom of page