top of page

ዝማሬውንና ምስጋናውን በጀመሩ ጊዜ . . .

እግዚአብሔርን ከዙፋኑ ያንቀሳቀሰና የንጉሱንና የሕዝቡን ዉጊያ እግዚአብሔር ተክቶ የተዋጋበትንና ከየአቅጫው የተነሱ ጠላቶቻቸውን አሳልፎ እንዲሰጡ ያደረገ በንጉሣቸው ኢዮሣፍጥና በይሁዳ ሕዝብ የተከናወነውን ድርጊት በ2ኛ ዜና መዋልዕ መጽሐፍ መዕራፍ 20 ላይ እንመለከታለን።

በዚያን ዘመን የሞአብና የአሞን ልጆች ላይ ሞአባውያንን ጨምሮ እጅግ በክፋ ሁኔታ ሰራዊቶቻችዉን ጭነው ሊወጉት እንደመጡ ኢዮሣፍጥ ባውቀ ጊዜ ጦሩን ሰብቆ፤ የጦር አዛዦቹን አሰባስቦና ክተት አውጆ ሳይሆን በአመታት ሁሉ ሲረዳቸውና ከጠላቶቻችው እየታደጋቸው ያኖራቸውን እግዚአብሔርን ለመፈልግ ፊቱን በማቅናት ነበር ምላሽ የሰጠው። እንዲሁም ምላሹ በጾምና በጸሎት በመሆን “አቤቱ አባታችን” በማለት እግዚአብሔር በዘመናቸው ያደረገላቸውን፣ ስለማንነቱና ስለክብሩ ተራ በተራ በጉባኤ መሃል ቆሞ በመዘርዘርና በማመስገንም ነበር።

አቤቱ የአባታችን አምላክ ሆይ “በሰማይ ያለህ አምላክ አንተ አይደለህምን? የአሕዛብንስ መንግሥታት ሁሉ የምትገዛ አንተ አይደለህምን? ኃይልና ችሎታ በእጅህ ነው፥ ሊቋቋምህም የሚችል የለም ... ለወዳጅህም ለአብርሃም ዘር ለዘላለም የሰጠሃት አንተ አይደለህምን? ...” በማለት ሲጠይቁት፣ ሲያመሰግኑትና ሲማጸኑት የእግዚአብሔር መንፈስ በየሕዚኤል በኩል ወደ ጉባኤዉ መጣ።

እንዲህም አለ፦ “... ሰልፉ የእግዚአብሔር ነው እንጂ የእናንተ አይደለምና ከዚህ ታላቅ ወገን የተነሣ አትፍሩ፥ አትደንግጡም” በማለት ማድርግ ያለባቸውንም ምሪት ጭምር ሰጣቸው። ቃል ከአሪያም ሲወጣ ኢዮሣፍጥና ህዝቡ በግምባራቸው በምድር ላይ በመደፋት ፈጣሪያችዉን አመሰገኑ።

ከጾም ጸሎት በተጨማሪ፤ እግዚአብሔር ያደረገላቸውን ከመዘርዘርም ባለፈ ጌጠኛ ልብሶቻችውን ለብሰው “ምህርቱ ለዘላለም ነውና እግዚአብሔርን አመስግኑ” እያሉ ዝማሬውንና ምስጋናውን በጀመሩ ጊዜ ይሁዳን ሊወጉ በመጡት በአሞን፣ በሞዐብና በሰይርም ሰዎች ላይ እግዚአብሔር ድብቅ ጦርን አመጣባቸው፤ እነርሱም ሞቱ። ህዝቡና እዮሣፍጥ በበገና፣ በመስንቆና በመለከትም ወደ ኢየሩሳሌም ወደ እግዚአብሔር ቤት ተመለሱ።

ወንድሞቼና እህቶቼ በግልም ሆነ በጋራ ሆነን የሰማይ መስኮቶችን አስከፍተን ድምጽ የምንሰማበት፣ ምሪትም የምንቀበለዉና ለችግሮቻችን መፍትሄ የምናገኘው የችግሮቻችንን ብዛትና ጥልቀት፤ የጠላቶቻችንን ክፋትና ብዛት በመዘርዘርና በማግዘፍ አይደለም።

ነገር ግን በጾምና በጸሎት በመሆን በገናችንን አንስተን ሰማይንና ምድርን በክንዱ የለካውን፣ እነክሩቤል ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እያሉ ያለማቋረጥ የሚሰግዱለትን አብን እያመለክን የነገስታት ንጉስ፤ የይሁዳ አንበሳ የሆነውን በሞቱ ህይወትን፤ በመገረፉ ቁስል ፈዉስን የሰጠንን ኢየሱስ እየዘመርን የዛሬውንም ተራራ እንንዳለን አዲሲቷንም ጺዮን እንወርሳልን። አሜን።


Recent Posts
Archive
Search By Tags
No tags yet.
Follow Us
  • Facebook Basic Square
  • Twitter Basic Square
  • Google+ Basic Square
bottom of page