top of page

መጠበቅና መጠባበቅ

ሰው ተስፋ ያደረግውን ማንኛውንም ነገር የመጠበቅ ዝንባሌ አለው። መጠበቅ በራሱ ክፋት የለውም። በሌላ መልኩ በእጅ ያለውን፣ የተያዘውን መጠበቅ ወይንም መንከባከብም ተገቢ ነው። ቀጠሮ የተቆረጠለትን፤ ቀንና ሰአት የተወሰነለትን ነገር መጠበቅም መጥፎም አይደለም። ነገር ግን በመጠበቅ ውስጥ መዘግየት አለ። የሁኔታዎች መዘግየት ደግሞ ዝለት፣ ዝንጉንትን፣ ቁጣንና ተስፋ መቁረጥን ይወለዳል። መጠባበቅ ውስጥ ግን መታደስ፣ መዘጋጀት፣ ተስፌኛንትና መበርታት አሉት። እነዚህም የመጠባበቅ መለያ ባሂሪያቶቹ ናችው።

በሉቃስ ወንጌል መዕራፍ 15:25-32 ጠፍቶ ስለተግኘው ልጅ ሳይሆን ለገዛ አባቱ እንደ ተቀጣሪ ዘመኑን በሙሉ ያገለገል የታላቅ ልጅ ታሪክ እናያለን። ይህ ታላቅ ልጅ አባቱን ሲያገለግል የከርመው አንድ ቀን ድርሻውን ከአባቱ ለመቀበል በመጠበቅ ስሌት ነበር። የዚህ ወንድም መጠበቅ በደስታ ሰአት እንዲቆጣ እንዳደረገውና አባቱንም ጠርቶ እስከ ዛሬ ሳገለግልህ ከባልንጀሮቼ ጋር እንድደሰት የፍየል ግልገል እንኳን አልሰጠሄኝም ብሎ አባቱ ያልግመተውን ዱብ እንዳደረገ እናያለን። ልብ ስንል አባቱ ለልጁ ያሰበለት ግን እጅግ ከፍ ያለና ከተራ የፍይል ግልገል እጅግ የላቀ መሆኑንም እንገነዘባለን (ሉቃስ 15:31-32)።

የአስሩን ልጃገረዶች ታሪክ በማቴዎስ ወንጌል 25፤ 13 ደግሞ ስንመለከት አምስቱ ይጠብቁ አምስቱ ድግሞ ይጠባበቁ እንደነበረ እንርዳለን። ምክንያትም “አምስቶቹ ልጃገረዶችህ እየተጠባብቁ ስለነበረ መጠባበቂያ ዘይት በማሰሮ ይዘው በንቃት ይጠባቁ ነበር። ቀኒቱና ሰአቲቱን አታውቁምና ንቁ”(ማቴዎስ 25:13)።

ነገር ግን የሙሽራው የመምጣቱ ደውል ሲመታ ሲጠባበቁ የነበሩት መብራታቸውም ተርኩሰው ከሙሽራው ጋር ወደ ሰርጉ ቦታ እንደገቡና አብረውም እንደታደሙ እናያለን። እንግዲህ መሽራው እንድሚመጣ እንጂ መቺ እንደሚመጣ አልተነገራቸውም። ከክፍሉ እንድምንረዳው መዘግየቱ ራሱ የታውቀው እኩለ ሌሊት በማለፉ ነበር። እነሱ ግን ዝግጁ ነበሩ።

ልብ እንበል ቀን ያልተቆረጠለትን ተስፋ የምናድርገውንም ነገር መጠበቅ አንችልም። ምክንያቱም የሚጠብቅ ይዘነጋል፤ይዝላል፤ተስፋ ይቆርጣል ከዚያም ሲያልፍ አይዘጋጅም። እነዛ አስተዋዮቹ ልጃግርዶች ግን መጠባበቂያ ከመያዛችውም ባሻግር የባሰ ቢመጣ ብለው ተጨማሪ ዘይት የሚገዛበትን ቦታ ሁል እንድሚያውቁ እረዳለሁ።

እኛ አማኞች ክርስቶስ ዳግም እንደሚመጣ አጥብቀን እናውቃልን። የመምጣትንም ምልክቶች ከቅዱስ ቃሉ ተምረናል። ቀኑና ሰአቱን ስለማናውቅ እንድንዘጋጅ ነው ትዕዛዝ የተቀበልነው። ስለዚህ መጠበቅ ሳይሆን መጠባበቅ ነው ያለብን። ስንጠባብቅ ቀንዳችን ከፍ ከፍ ይላል። መጠባብቅ ተስፋ አለውና የቀናትና የሰአታት ሉጋም አይገድቡትም። ሁሌም በአዲስ ሃይል አዲስ እየሆንን እንጓዛለን።

መጽሐፍ ቅዱሳችንም በኢሳያስ 40፡31 “እግዚአብሄርን በመተማምን የሚጠባበቁ ግን ኃይላቸውን ያድሳሉ፤እንደንስር በክንፍ ይወጣሉ ይሮጣሉ፣አይታክቱም ይሄዳሉ፤አይደክሙም”ይልናል። ተስፋ የምናደርግም እየሱስ በእርግጥም ይመጣል ነገር ግን ቀንና ሰአቱን ልናውቅ አልተፈቀደልንምና ሃይላችን እንዲታደስ፤ በክንፍ እንድንወጣ እንዳንደከም ከመጠብቅ ህይወት ወደ መጠባብቅ ህይወት በጋር እንሽጋገር። እግዚአብሄርም ይርዳናል። አሜን።


Recent Posts
Archive
Search By Tags
No tags yet.
Follow Us
  • Facebook Basic Square
  • Twitter Basic Square
  • Google+ Basic Square
bottom of page