top of page

እኔን እግዚአብሔር ፍቅር እንደሆንኩ ኣታውቅም? ብታውቀኝ እና ብታምንብኝ ኖሮ ባልፈራህ ነበር

እኔ ፍቅር ነኝ!!! ፍጹም ፍቅር ፍርሃትን አውጥቶ ይጥላል እንጂ በፍቅር ፍርሃት የለም

 1ኛ የዮሐንስ መልእክት 4፡8 & 1ኛ የዮሐንስ መልእክት 4፡18

ትንቢተ ኢሳይያስ

​35፡4

ፈሪ ልብ ላለህ። እነሆ፥ እኔ አምላክህ በበቀል በእግዚአብሔርም ብድራት እመጣለሁና፥ መጥቼም ኣድንሀለውና በርታ፥ አትፍራ።

መጽሐፈ ኢያሱ 

1፡9

በምትሄድበት ሁሉ አምላክህ እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ነኝና ጽና፥ አይዞህ፤ አትፍራ፥ አትደንግጥ ብዬ አላዘዝሁህምን?

ትንቢተ ኢሳይያስ

​43፡1

አሁንም ያዕቆብ ሆይ፥ የፈጠረህ፥ እስራኤልም ሆይ፥ የሠራህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል። ተቤዥቼሃለሁና አትፍራ፤ በስምህም ጠርቼሃለሁ፥ አንተ የእኔ ነህ።

መዝሙረ ዳዊት

27፡1

እግዚአብሔር ብርሃኔና መድኃኒቴ ነው፤ የሚያስፈራኝ ማን ነው? እግዚአብሔር የሕይወቴ መታመኛዋ ነው፤ የሚያስደነግጠኝ ማን ነው?

1ኛ የጴጥሮስ 

5፡7​

እርሱ ስለ እናንተ ያስባልና የሚያስጨንቃችሁን ሁሉ በእርሱ ላይ ጣሉት።

ትንቢተ ኢሳይያስ 

​41፡10

እኔ ከአንተ ጋር ነኝና አትፍራ፤ እኔ አምላክህ ነኝና አትደንግጥ፤ አበረታሃለሁ፥ እረዳህማለሁ፥ በጽድቄም ቀኝ ደግፌ እይዝሃለሁ።

bottom of page