እኔ እግዚአብሔር ፈውሼሃለው እመን ብቻ
ኣምነህ በጸሎት የለመንከኝን ሁሉ ትቀበላለህ ። የማቴዎስ ወንጌል 21፡22
ኣባቴ እግዚኣብሄር ሆይ ተባረክ። በነገሮች ሁሉ በላይ ኣመሰግናለሁ።
ጌታና ኣባቴ ሆይ ይህ (በሽታ ወይም ህመም) ኣለብኝ። በቃልህ እንዲ ብለሃል (ጥቅስ) እንደቃልህ ፈውሰኝ። ኣባዬ በቃልህ እንዲህ ብለሃል " ኣምኜ በጸሎት የለመንኩትን ሁሉ ትቀበላለህ በየማቴዎስ ወንጌል 21፡22" ላይ። እኔም በልቤ ኣምኜ ጸለይኩ። ኣንተም አንደቃልህ ስለፈወስከኝ ኣመሰግናለሁ። በኢየሱስ ስም ኣሜን
መዝሙረ ዳዊት
6፡1፥2
አቤቱ፥ በቍጣህ አትቅሠፈኝ፥ በመዓትህም አትገሥጸኝ። ድውይ ነኝና አቤቱ፥ ማረኝ፤ አጥንቶቼ ታውከዋልና ፈውሰኝ።
መዝሙረ ዳዊት
107 ፡ 18፥20
ሰውነታቸው መብልን ሁሉ ተጸየፈች፥ ወደ ሞትም ደጆች ቀረቡ። በተጨነቁ ጊዜም ወደ እግዚአብሔር ጮኹ፥ ከመከራቸውም አዳናቸው። ቃሉን ላከ ፈወሳቸውም፥ ከጥፋታቸውም አዳናቸው ።
መዝሙረ ዳዊት
147፡3
ልባቸውን የቈሰሉትን ይፈውሳል፥ ሕማማቸውንም ይጠግናል።
ትንቢተ ኢሳይያስ
53፡5
እርሱ (ኢየሱስ) ግን ስለ መተላለፋችን ቈሰለ፥ ስለ በደላችንም ደቀቀ፤ የደኅንነታችንም
ተግሣጽ በእርሱ ላይ ነበረ፥ በእርሱም ቍስል እኛ ተፈወስን።
ትንቢተ ኢሳይያስ
57፡18
መንገዱን አይቻለሁ እፈውሰውማለሁ፥ እመራውማለሁ፥ ለእርሱና ስለ እርሱም ለሚያለቅሱ መጽናናትን እመልሳለሁ።
ትንቢተ ኤርምያስ
30፡17
እኔ ጤናህን እመልስልሃለሁ ቍስልህንም እፈውሳለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር