top of page
እኔ እግዚአብሔር ጤንነትን ሰጥቼሃለው ቃሌን ጠብቅ በእምነትም ውሰድ
እኔን አምላካህን እግዚአብሔር ኣምልከኝ ፥ እኔም እህልህንና ውኃህን እባርካለው በሽታንም ከመካከልህ አርቃለሁ። በምድርህም መካን ወይም የምትጨነግፍ አትሆንም፤ የዘመንህን ቍጥር እሞላለሁ።
1ኛ ወደ ጢሞቴዎስ
4፡8
ሰውነትን ለሥጋዊ ነገር ማስለመድ (እስፖርት መስራት) ለጥቂት ይጠቅማልና፤ እግዚአብሔርን መምሰል ግን የአሁንና የሚመጣው ሕይወት ተስፋ ስላለው፥ ለነገር ሁሉ ይጠቅማል።
5፡15
እኔ እግዚአብሔር ሕማምን ሁሉ ከአንተ ኣርቃለሁ፤ የምታውቀውንም ክፉውን የግብፅ በሽታ ሁሉ በአንተ ላይ አያደርስብህም፥ በጠላቶችህም ሁሉ ላይ ኣመጣባቸዋለሁ።
መጽሐፈ ምሳሌ
16፡23፥24
የጠቢብ ልብ አፉን ያስተምራል፥ ለከንፈሩም ትምህርትን ይጨምራል።
ያማረ ቃል የማር ወለላ ነው፤ ለነፍስ ጣፋጭ ለአጥንትም ጤና ነው።
መጽሐፈ ምሳሌ
3፡7፥8
በራስህ አስተያየት ጠቢብ አትሁን፤ እግዚአብሔርን ፍራ፥ ከክፋትም ራቅ፤
ይህም ለሥጋህ ፈውስ ይሆንልሃል፥ ለአጥንትህም ጠገን።
መጽሐፈ ምሳሌ
4፡20፥22
ልጄ ሆይ፥ ንግግሬን አድምጥ ወደ ቃሌም ጆሮህን አዘንብል። ከዓይንህ አታርቃት፥ በልብህም ውስጥ ጠብቃት።
ለሚያገኙአት ሕይወት፥ ለሥጋቸውም ሁሉ ፈውስ ነውና።
bottom of page