እግዚአብሔር ይላል
ኃጢአትን ሠርተሃልና የኔ የእግዚአብሔርም ክብር ጎድሎሃል ወደ ሮሜ ሰዎች3፤23 የኃጢአትህ ደመወዝ ሞት ነው ወደ ሮሜ ሰዎች6፤23 ግን አተን ትንታግ ከእሳት ነጠኩሁ ትንቢተ ዘካርያስ 3፡2 ላንተ የጸጋ ስጦታዪ በክርስቶስ ኢየሱስ የዘላለም ሕይወት ነው። ወደ ሮሜ ሰዎች6፤23 ከተቀበልክ
የሐዋርያት ሥራ
16፡31
በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ እመን አንተና ቤተ ሰዎችህ ትድናላችሁ
ወደ ጢሞቴዎስ 2 1:9
ያዳነን በቅዱስም አጠራር የጠራን እግዚአብሔር ነውና፥ ይህም እንደ ራሱ አሳብና ጸጋ መጠን ነው እንጂ እንደ ሥራችን መጠን አይደለም፤ ይህም ጸጋ ከዘላለም ዘመናት በፊት በክርስቶስ ኢየሱስ ተሰጠን፥
ወደ ዕብራውያን 9: 28
እንዲሁ ክርስቶስ ደግሞ፥ የብዙዎችን ኃጢአት ሊሸከም አንድ ጊዜ ከተሰዋ በኋላ፥ ያድናቸው ዘንድ ለሚጠባበቁት ሁለተኛ ጊዜ ያለ ኃጢአት ይታይላቸዋል።
ወደ ሮሜ ሰዎች
1:16
ወደ ሮሜ ሰዎች
5:10
በወንጌል አላፍርምና፤ አስቀድሞ ለአይሁዳዊ ደግሞም ለግሪክ ሰው፥ ለሚያምኑ ሁሉ የእግዚአብሔር
ኃይል ለማዳን ነውና።
ጠላቶች ሳለን ከእግዚአብሔር ጋር በልጁ ሞት ከታረቅን፥ ይልቁንም ከታረቅን በኋላ በሕይወቱ እንድናለን፤
ወደ ሮሜ ሰዎች
10:9-11
ኢየሱስ ጌታ እንደ ሆነ በአፍህ ብትመሰክር እግዚአብሔርም ከሙታን እንዳስነሣው በልብህ ብታምን ትድናለህና፤
ሰው በልቡ አምኖ ይጸድቃልና በአፉም መስክሮ ይድናልና። መጽሐፍ። በእርሱ የሚያምን ሁሉ አያፍርም ይላልና።