top of page

ሰውና ጊዜ

አምና ሲሆን ዘንድሮ፣ ታሮጌው ተርታ ተደምሮ፣ ከትዝታ ጓዳ ሰምሮ፣ ታሪክ ሲባል ዞሮ፣ አዲሱ ሲጀመር ያለው ተገባዶ፣ ሽው ያለ ሲመስል ያለ መሰናዶ፣ ላልተገራበቱ በቁጭት ቀፍድዶ፣ ጊዜ አለፈ፣ ነጎደ ይላል ሰው … ወይ ነዶ! ወይ ነዶ! ሰው አለፈ ይላል ጊዜ … ከንቅልፉ ተዛምዶ፤ መታከትን ወዶ። ሲሰራበት ደግሞ ሲቆጥረው ከወርቅ፣ በወቅቱ መገለጥ በጥበብ ሲታጠቅ፣ የአሁን ሐሳብ ሲለይ የሰማይ መልክ እንዲያውቅ፣ በኢሳኮር መረዳት በመገለጥ ሲመጥቅ፣ በዳንኤል ጽድቅ ትጋት፣ ባሁን እውቀት ሲታጠቅ፣ በአሴር ባርኮት፤ ኃይል ከጊዜው ጋር ሲልቅ፣ በአርአያ ካሌብ እምነት፤ የብርታት ጉልበት ሲጠበቅ፣ በዳዊት ቅንነት፤ ልብ ካምላክ ልብ ሲጣበቅ፣ ቀኖቹን መነዘርኩ ገንዘቤ አረኳቸው፣ በማያልፍ ሃሳብ አድምጄ ያዝኳቸው፣ ከድካም ወጥቼ በብርታት ውስጥ ናኘሁ፣ ቀኖቼን ማረኩኝ ጊዜዬን ተቤዠው፣ በመክሊት ቀኖቼ አተረፍኩ ይላል ሰው። የታተረበቱን ዞር ብሎ ሲያየው። የተጠራበትን በጊዜው ሲኖረው።


Recent Posts
Archive
Search By Tags
No tags yet.
Follow Us
  • Facebook Basic Square
  • Twitter Basic Square
  • Google+ Basic Square
bottom of page