top of page

ጸሎት አስተምረን -- የእለት እንጀራ (ክፍል አስራ-አንድ)

“እርሱም በአንድ ስፍራ ይጸልይ ነበር፥ በጨረሰም ጊዜ ከደቀ መዛሙርቱ አንዱ፦ ጌታ ሆይ... እንጸልይ ዘንድ

አስተምረን አለው። አላቸውም፦ ስትጸልዩ እንዲህ በሉ፦ በሰማያት የምትኖር አባታችን ሆይ... የዕለት እንጀራችንን ዕለት

ዕለት ስጠን…” (ሉቃ. 11፡3)

ጌታ ባስተማረው ጸሎት ውስጥ የእግዚአብሔርን አባትነት እና የኛን ልጅነት መሰረት አድርገን እንቀርባለን።

ደግሞም ስሙ በሕይወታችን እንዲቀደስ (የከበረውን ስፍራ እንዲይዝ) እንጸልያለን። መንግስቱም እንድትመጣና

በመካከላችን ጽድቁ፣ ሰላሙና ደስታው እንድትሆን እንጸልያለን። በሰማይ ፍጹም የሆነችው ፈቃዱም በምድር

እንድትሆንና እኛም የእርሱን ፍቃድ አውቀን ወደ ፈቃዱ እንድንገባም እንጸልያለን። ዛሬ እንደምናየው ደግሞ እግዚአብሔር

የእለት እንጀራችንን ዕለት ዕለት እንዲሰጠንም እንጸልያለን።

እያንዳንዷ ቀን ከእግዚአብሔር የምትሰጥ የጸጋ ቀን ነች። በየለቱም የምንወጣውና የምንገባው በእርሱ ጸጋ

ተደግፈን ነው። ስለዚህም ለእለቱ ስለሚያስፈልገን “እንጀራ” መጸለይ ተገቢ ነው። ስለ እለት እንጀራ ስንጸልይ በየለቱ

ለህይወታችን የሚያስፈልገውን ሁሉ የሚጠቀልል ነው። በእርግጥ በዚህ በመዕራቡ ዓለም መብልና መጠጥ እንደ ትልቅ

ጉዳይ ባይቆጠርም እኛ ግን ፍጥረትን ሁሉ የሚመግበውና እህል ውሃን የሚባርከው እግዚአብሔር አባታችን እንደሆነ

ተረድተን በምስጋናና በጸሎት መቅረብ አለብን። “የዕለት እንጀራ” ጸሎት ለየለቱን መብልና መጠጥ አንስቶ በቀኑ ላይ

ለመውጣትና ለመግባት የሚያስፈልገንን ሁሉ የሚጠቀልል ጸሎት ነው። በእለቱ ስለሚያስፈልገን ጸጋ እንጸልያለን። ለቀኑ

የሚያስፈልገን ጸጋ ለኛ የምንኖርበት የእለት እንጀራችን ነው። እግዚአብሔር ዙፋኑ የጸጋና የምሕረት ዙፋን ነው።

በእምነት ወደ ፊቱ ቀርበን ጸጋንና ምህረትን ስንጠይቅ ተቀብለን እንነሳለን። ለእለቱ ስራችን፣ ለእለቱ የልጆቻችን

የትምህርት ቤት ውሎ፣ ለእለቱ የቤታችን ጉዳይ ጸጋን መጠየቅ ማስተዋል ነው። ጸጋ ማለት ለማይገባቸው የሚሰጥ

የእግዚአብሐእር ችሮታ ነው። ያለ ጸጋ በራሳችን ነን፤ ጸጋ ሲሰጠን ግን በእግዚአብሔር ችሎታ ውስጥ እንገባለን። በእለቱ

ስለሚያስፈልገን ጥበቃ ስንጸልይ ለእለት እንጀራ እየጸለይን ነው። ቀኑ በራሱ በክፋት የተያዘ ነው። በቀኑ ውስጥ በድል

ለመመላስ እለት እለት በእግዚአብሔር ጥበቃ ውስጥ መሆን አለብን። በእለቱ ስለሚያስፈልገን ሞገስ መጸለይ አለብን።

የእግዚአብሔር ሞገስ በድልነሺነት ያመላልሰናል።

ለኛ የእለት እንጀራችንን የሚሰጠን እግዚአብሔር ነው። እያንዳንዷን ቀን የምንኖረው በርሱ ላይ ታምነንና

ተደግፈን ነው። የትላንት መና ለዛሬ አይሆንም። መናው በየእለቱ መለቀም አለበት። የእለት እንጀራችንን በየለቱ

የሚሰጠን እርሱ ነው። ስለ ትላንቱ እንጀራ እያመሰግንን፣ ስለዛሬው እንጸልያለን። ስለነገው ደግሞ በርሱ እንታመናለን።

አቤቱ የዕለት እንጀራችንን ዕለት ዕለት ስጠን። አሜን!


Recent Posts
Archive
Search By Tags
No tags yet.
Follow Us
  • Facebook Basic Square
  • Twitter Basic Square
  • Google+ Basic Square
bottom of page