top of page

የማይሻገረው እንዳይሻገር!

“በሃይማኖት ብትኖሩ ራሳችሁን መርምሩ፤ ራሳችሁን ፈትኑ፤ ወይስ ምናልባት የማትበቁ ባትሆኑ፥ ኢየሱስ ክርስቶስ በእናንተ ውስጥ እንዳለ ስለ እናንተ አታውቁምን?

(2ቆሮ 13፡5) እንኳን ጌታ ለ2018 ዓመተ ምህረት ዋዜማ በሰላም አደረሳችሁ። ቀናት ቀናትን

ወልደው አሮጌ አመት አልፎ በአዲስ አመት ሲተካ በቸርነቱ አመትን የሚያቀዳጀውን እግዚአብሔርን እናመሰግናለን። (መዝ. 65፡11) እያንዳንዱ አመት ከርሱ የምንቀበለው ጸጋና በረከት ነው። ዘመንን፣ እድሜን የሚሰጥ እርሱ ነው። ካሌብ ሕይወቱን ዞር ብሎ ተመልክቶ “እነዚህን አርባ አምስት ዓመት በሕይወት አኖረኝ” (ኢያሱ 14፡10) በማለት ለኖረበት ዘመንና ለተሰጠው እድሜ እግዚአብሔርን ያመሰግናል። እኛም ለተሰጠን አዲስ አመት፤ ለተጨመረልን እድሜ እግዚአብሔርን ማመስገን አለብን። አሁንም ስለምንገባበት አዲስ አመት እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን።

አዲስ አመት በመጣ ቁጥር ብዙ ሰዎች የአዲስ አመት ውሳኔ ያሳልፋሉ። እንዳንዶች ክብደት ለመቀነስ፣ ሌሎች አካላዊ እንቅስቃሴ ለማድረግ፣ ሌሎች ደግሞ ከተለያዩ ልማዶችና ሱሶች ነጻ ለመሆን ለራሳቸው ቃል ይገባሉ። ይህ በተግባር ላይ ከዋለ መልካም ነገር ነው። ነገር ግን ብዙ ጊዜ እንደሚስተዋለው እንደዚህ አይነቱ ውሳኔ እጅግም አይዘልቅም። እኛስ እንደ እግዚአብሔር ልጆች ወደ አዲሱ አመት ስንገባ ምን እያሰብን ይሆን? የበለጠ ቃሉን ለማንበብ? የበለጠ ለመጸለይ? የበለጠ ሕብረት ለማድረግ? የበለጠ በአግልሎት ለመትጋት? መልካም ነው። በምናስበው አቅጣጫ እንከናወን ዘንድ እግዚአብሔር ጸጋውን ያብዛልን።

በአንጻሩ ደግም ወደ አዲሱ አመት ስንገባ እራሳችንን ቆም ብለን መመርመርና መፈተሽ መልካም ነው። መጽሐፍ “በሃይማኖት ብትኖሩ ራሳችሁን መርምሩ” ይለናል። እስቲ ቆም ብለን ወደ 2018 አብረውን ማለፍ የለባቸውም የምንላቸውን ነገሮች እናስብ። ምንድን ነው ካሮጌው አመት ጋር መቅረት ያለበት? ቅያሜ ካለን ቅያሜን ይዘን ወደ አዲሱ አመት አንሻገር። ቅያሜን ካሮጌው አመት ጋር ጥለነው በአዲሱ አመት ለአንዲስ ግንኙንት እንነሳሳ። ቶሎ የሚከበን የኃጢያት ልምምድ ካለ ተከትሎን ወደ አዲሱ አመት እንዳይሻገር በጌታ ፊት ጸጋን ብንጠቅ መልካም ነው። ወደ አዲሱ አመት ስንዘልቅ ከድካሞቻችን ጋር እንፋታ። ዳተኝነትን ጥለን ትጋትን ለመታጠቅ እንወስን። ማስንቆአችንን ይሰቀልን እናውርድ። ሰይፋችንን የጣልን እናንሳ። “እኔ ካባቶቼ አልበልጥም ብለን” ከክትክታ ዝፍ ስር የተኛን እንነሳ። ልብ እንበል እግዚአብሔር በልባችን ስንወስን ጸጋና ሞገስን ይሰጠናል።


Recent Posts
Archive
Search By Tags
No tags yet.
Follow Us
  • Facebook Basic Square
  • Twitter Basic Square
  • Google+ Basic Square
bottom of page