ሙት አያመሰግን & ተከፍቷል ሰማይ
- Redeatu G. Kassa
- Jul 28, 2018
- 1 min read
ሙት አያመሰግን
እፍ ያለብህ እስትንፋስ
ከስጋህ ሳትገሰስ
ህያው ነፍስ
አምልክ ፈጣሪን
ሙትማ አያመሰግን::
ውደድ እያለህ
ሳይሰበሰብ ገመድህ
አፈር ሳይቀምስ ኣፈር
እያሉ ነው ማፍቀር::
ተከፍቷል ሰማይ
ለአዳም ልጆች አርነት
ወልድ ሲሰቃይ
በሰው ልጅ መስዋእት
ተከፍቷል ሰማይ::
(አዎ ጌታችን በመስቀል ሲውል ሰማይ ከፍቶት ነበር:: ፀሃይ ጨለመች:: ደግም እርሱ የሃጢያት መስዋእት ሆኖ ለተቀበሉት ሁሉ በስሙ ላመኑት የሰማይን በር ከፍቷል::)
Comments