ስለ አራቱ መንፈሳዊ ሕጎች ሰምተዋል?
አንድ፦ እግዚአብሔር ስለሚያፈቅረን ለሕወታችን አስደናቂ እቅድ
ሰጥቶናል። “በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና።” ዮሐንስ 3፡16
ሁለት፦ ሰው ኃጢአተኛ የሆነ ባህርይ ስላለውና በዚህም ምክነያት ከእግዚአብሔር ስለ ተለየ እግዚአብሔር ለእርሱ ያለውን ፍቅርና እቅድ ሊለማመድ አይችልም። “ሁሉ ኃጢአትን ሠርተዋልና የእግዚአብሔርም ክብር ጎድሎአቸዋል።”ሮሜ 3፡23
ሶስት፦ ኢየሱስ ክርስቶስ ለኛ በመሞቱ በእርሱ በኩል ብቻ ሰው ወደ እግዚአብሔር ይደርሳል። “እኔ መንገድና እውነት ሕይወትም ነኝ፤ በእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም።” ዮሐንስ 14፡6
አራት፦ ኢየሱስ ክርስቶስን እንደ አዳኛችንና ጌታችን አድርገን በመቀበል እግዚአብሔር አምላክ ለኛ ያለውን ፍቅርና እቅድ ልናውቅና ልንለማመድ እንችላለን።“ለተቀበሉት ሁሉ ግን፥ በስሙ ለሚያምኑት ለእነርሱ የእግዚአብሔር ልጆች ይሆኑ ዘንድ ሥልጣንን ሰጣቸው።” ዮሐንስ 1፡12
ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን እንደ ግል አዳኞ አድርገው ለመቀበል ከወሰኑ የሚከተለውን የንስሃ ጸሎት ይጸልዩ ዘንድ እናበረታታዎታለን።
“እግዚአብሔር ሆይ ዛሬ የደህንነትን ወንጌል እንድሰማ እድልን ስለሰጠኽኝ አመሰግንሃለው። እኔ ኃጢያተኛ ሰው ነኝ። ዛሬ ከቅድስት ድንግል ማሪያም ተወልዶ ስለኔ ኃጢያት በመስቀል የሞተውን፣ በሶስተኛውም ቀን ከሞት የተነሳውን ልጅህን ኢየሱስ ክርስቶስን የግል አዳኜ አድርጌ እቀበላለሁ። በልጅህ በኢየሱስ ክርስቶስ ደም ከአጢያቴ ሁሉ አንጻኝ፤ ቀድሰኝ፤ ልጅህ አድርገኝ፤ በመንፈስ ቅዱስም ማህተም አትመኝ። ስላደረክልኝ ምሕረት አመሰግንሃለሁ። በኢየሱስ ክርስቶስ ስም። አሜን!”