top of page

ሌላ አጽናኝ

“ብትወዱኝ ትእዛዜን ጠብቁ። እኔም አብን እለምናለሁ ለዘላለምም ከእናንተ ጋር እንዲኖር ሌላ አጽናኝ ይሰጣችኋል።” ዮሐ. 14፡15-16

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የምድር አገልግሎቱን ፈጽሞ ወደ አባቱ ከመሄዱ በፊት አንድ ታላቅ ተስፋ ሰጥቶናል። ጌታ እርሱ ከሄደ በኋላ ሌላ አጽናኝ እንደሚመጣልን ተናግሮን ነበር። ህይ “ሌላ አጽናኝ” የተባለው መንፈስ ቅዱስ ነው። እርሱ እንደ ኢየሱስ ያለ ሌላ አጽናኝ ነው። “ሌላ” የሚለው ቃል አዲስ ኪዳን በተጻፈበት በክሪክ ቋንቋ “allŏs” ማለት ሲሆን ትርጉ ደግም “another of the exact, identical, specific kind without one single variation” ማለት ነው። ይህ እንግዲህ የሚያመለክተው መንፈስ ቅዱስ ልክ እንደ እየሱስ ያለ ሌላ አጽናኝ እንደሆነ ነው። ስለሆነም ኢየሱስ ፊተኛው አጽናኝ ሲሆን መንፈስ ቅዱስ ደግም ሌላው አጽናኝ ነው። “አጽናኝ” ለሚለው ቃል የእንግሊዝኛው አቻ ቃል “Comforter” የሚለው ሲሆን ሁለቱም ቃላት “ፒራቅሊጦስ” ወይንም “Counselor” ለሚለው ቃል የተሰጡ ፍቺዎች ናቸው። ይህ ማለት ደግም አማካሪ፣ የሕግ ረዳት፣ በሁሉም ጉዳይ የሚፈለግን ሰው የሚገልጽ ነው። እንዲሁ መንፈስ ቅዱስ በሁሉም ጉዳይ ምንፈልገው፣ የምንጠጋው፣ የምንጠይቀው፣ ሁልጊዜም አብሮን የሚቆም ጠበቃችን፣ መሪያችን፣ አማካሪያችን ነው። ልክ ባለጉዳይ በችሎት ፊት በጠበቃው እንደሚናገር ሁሉ መንፈስ ቅዱስም ሁል ጊዜ በሚያስፈልገን ነገር ሁሉ አብሮን አለ። ለዚህ ነው ቅዱሳኑ በመንፈስ ቅዱስ ተነድተው ማንም በማይቋቋመው ጥበብና ኃይል ይናገሩ የነበሩት። ይህ ሌላው አጽናኝ ከእኛ ጋር እና በኛ ውስጥ ያለ ነው። በብሉይ ኪዳን መንፈስ ቅዱስ ከእግዚአብሔር ሰዎች ጋር አብሮ ይሆን ነበር። ያነቃቃቸውና ታላላቅ ነገሮችንም ያደርጉ ነበር። በአዲስ ኪዳን ኢየሱስ ሞትን አሸንፎ ከፍ ከፍ ስላለ መንፈስ ቅዱስ አሁን ያለው ከኛ ጋር ብቻ ሳይሆን በኛ ውስጥም ነው። ጌታ በምድር በነበረበት ጌዜ የቃሉን ሚስጢር እየገለጠ፣ በአጋንንት የተያዙትን ነጻ እያወጣ፣ ድውያንን እየፈወሰ፣ የመንግስቱን ወንጌል እየሰበከ — በአጠቃላይ የአባቱን የአብን ፍቃድ እያደረገ ተመላልሷል። ሐዋሪያቱና ደቀ መዛሙርቱ በሁሉ ነገር ዘወር ብለው ይመለክቱ የነበረው ጌታን ነበር። እምነታቸው ሲናወጥ ወደ እርሱ ተመልክተው ይጽናናሉ። ጥያቄ የሆነባቸውን ነገር ሁሉ ወደ እርሱ ያቀርባሉ። ድውያናቸውንና ሙታናቸውን በእግሩ ስር ያስቀምጣሉ። በሰርጋቸው ላይ በመገኘት ጉድለታቸውን ሞልቷል፤ በለቅሶአቸው ላይ አብሮ አዝኖ አጽናንቷል፤ የተራቡትን መግቧል። መንፈስ ቅዱስ “ሌላ አጽናኝ” ሆኖ ይህንን ጌታ የጀመረውን ስራ ሊቀጥል ነው የመጣው። ሐዋሪያቱ በነገር ሁሉ ወደ ጌታ ዘወር ይሉ እንደነበር እኛም በነገር ሁሉ ወደ መንፈስ ቅዱስ ዘወር እንል ዘንድ ያስፈልገናል። አሁን ከቤተ ክርስቲያን ጋር ያለው እርሱ ነውና።


Recent Posts
Archive
Search By Tags
No tags yet.
Follow Us
  • Facebook Basic Square
  • Twitter Basic Square
  • Google+ Basic Square
bottom of page