top of page

ተቀብተናል

“በክርስቶስም ከእናንተ ጋር የሚያጸናንና የቀባን እግዚአብሄር ነው....” 2ቆሮ. 1፡21-22“እናንተም ከቅዱሱ ቅባት ተቀብላችሗል ሁሉንም ታውቃላችሁ....ከእርሱ የተቀበላችሁት ቅባት በእናንተ ይኖራል ማንም ሊያስተምራችሁ አያስፈልጋችሁም....” 1ዮሓ. 2፡20-22 እና 27

አብዛኛውን ጊዜ በቤተ ክርስቲያን አካባቢ “እከሌ የተቀባ አገልጋይ ነው....ወዘተ”~የሚለው ቃል የተለመደ ነው። ሰዎች መቀባትን ለተወሰኑ ጥቂት ገለሰቦች እንጂ ለራሳቸው የተገባ አድርገው አያስቡትም። እንዲሁም ተቀብታችሗል የተባሉትም ግለሰቦች እራሳቸውን ከሌሎቹ ምእምናን የተለዩ በማድረግ ልዩነትን ሲፈጥሩ ይስተዋላል። ይሁንና ከላይ የተመለከተው የመጽሃፍ ቅዱስ ክፍል ዛሬ በዚህ ዘመን እኛ ስለተቀቡት ሰዎች ከምናወራው እጅግ የተለየ ነው።ይህም በክርስቶስ የሆነ አማኝ ሁሉ ከቅዱሱ ቅባት የተቀበለ ወይም የተቀባ እንደሆነ እና ቅባቱ በ እርሱ እንደሚኖር ነው። ዛሬ ባለችው ቤተ ክርስትያን ያለው ከላይ የተጠቀሰው አመለካከት ግን የተወሰደው ቀድሞ በብሉይ ኪዳን ከነበረው የመቀባት ሂደት ነው።

እርግጥ ነው በቀድሞው ኪዳን እግዚአብሄር በእስራኤል ሕዝቦች መካከል የሚያገለግሉትን ካህናት እና ሕዝቡን የሚመሩትን ነገስታት ብቻ በመምረጥ እንዲቀቡ ያዝዝ ነበር። ለምሳሌ ለክህነት ከአሮንና ከልጆቹ እንዲሁም ከሌዋዉያን በስተቀር ማንም ሰው መቀባት አይችልም ነበር። በተጨማሪም በ እግዚአብሄር ማደሪያ ውስጥ ለአገልግሎት የሚውሉ እቃዎች ሳይቀሩ እንዲቀቡ እግዚአብሄር አዝዞአል (ዘጸ. 30፤ 25-33)። ሌላው እግዚአብሄር እንዲቀቡ የሚያዘው ነገታትን ነበር። ሕዝቡን የሚያወጡና የሚያገቡትን፤ ከጠላቶቻቸው የሚታደጉአቸውን ነገስታት እግዚአብሄር ከመረጠ በሗላ በነቢያቱ አማካይነት እንዲቅቡ በማድረግ በሕዝቡ ላይ እንዲሾሙ ያዝዝ ነበር። ይህ ደግሞ ሰዎችን ለክህነትም ሆነ ለንግስና ብቁ የሚያደርጋቸው ቅባቱ ብቻ እንደሆነ ያመለክታል። ስለዚህ በቀድሞው ኪዳን ዘመን እግዚአብሄር በመቅደስ የሚያገለግሉትን ካህናትም ሆነ ህዝቡን የሚመሩትን ካህናት ለራሱና እራሱ በመለየት እንዲቀቡ ያዝዝ ነበር። ይሁንና በአዲስ ኪዳን ይህ ሂደት ተቀይሮ የክህነቱም ሆነ የንግስናው ቅባት ከየትኛውም ነገድና ዘር ቢሆንም በክርስቶስ ኢየሱስ ለሆነ ሁሉ ተሰጠ።

እንግዲህ ወገኖች ከላይ በጥቅሱ ውስጥና በመልክቱ እንደተመለከታችሁት እንደ ብሉይ ኪዳን ዘመን እግዚአብሄር የተወሰኑ ሰዎችን ብቻ ለይቶ በነብያቶቹ አማካይነት በዘይት የቀባ ሳይሆን የተቀባውን ክርስቶስ ኢየሱስን በመቀበላችሁና መንፈስ ቅዱስ በእኛ በመሆኑ ምክንያት ቅዱሱ ቅባት በውስጣችን ነው፤ ወይም ተቀብተናል ማለት ነው። በብሉይ ኪዳን በተቀቡ ሰዎች ላይ ቅባቱ የሚያመጣው የራሱ ተጽዕኖና ሥራ እንደነበረው ሁሉ በአዲስ ኪዳንም በተቀባነው በእኛ ህይወት ለእግዚአብሄር በተሰጠንለትና በቅድስናችን መጠን ቅባቱ እየተገለጠ የሚሰራው የራሱ የሆነ ተግባር እንዳለው በሚቀጥለው ጽሁፍ የምንመለከተው ይሆናል።


Recent Posts
Archive
Search By Tags
No tags yet.
Follow Us
  • Facebook Basic Square
  • Twitter Basic Square
  • Google+ Basic Square
bottom of page