top of page

መንፈስ ቅዱስ አስተማሪው መንፈስ

“አብ በስሜ የሚልከው ግን መንፈስ ቅዱስ የሆነው አጽናኝ እርሱ ሁሉን ያስተምራችኋል.. ” (ዮሐ. 14፡ 25-26)።

መንፈስ ቅዱስ በኛ ከሚሰራቸው ስራዎች መካከል አንዱ ቃሉን ማስተማር ነው። የእግዚአብሔር መንፈስ የቃሉን ፍቺ ለአማኞች ያበራል። ጌታችንከላይበሰፈረውክፍል ይንንኑ አስተምሮናል። ስለዚህ ጉዳይ ሐዋሪያው ዮሐንስ ሲጽፍ “እናንተስ ከእርሱ የተቀበላችሁት ቅባት በእናንተ ይኖራል፥ ማንም ሊያስተምራችሁ አያስፈልጋችሁም፤ ነገር ግን የእርሱ ቅባት ስለ ሁሉ እንደሚያስተምራችሁ፥ እውነተኛም እንደ ሆነ ውሸትም እንዳልሆነ፥ እናንተንም እንዳስተማራችሁ፥ በእርሱ ኑሩ” በማለት ይመክረናል (1ዮሐ. 2:27)። እንዲሁም በብሉይ ኪዳን “ያስተምራቸውም ዘንድ መልካሙን መንፈስህን ሰጠሃቸው” (ነህ. 9:20) ተብሎየመንፈስቅዱስአስተማሪነትተገልጿል። ከቃሉእንደምንማረውመንፈስ ቅዱስ የቃሉ መምህር ነው።

መንፈስ ቅዱስ ሲስያስተምር በእግዚአብሔር ልብ ውስጥ ያለውን የቃሉን ሃሳብ ያበራልናል። የእግዚአብሔር ቃል በእግዚአብሔር ሰዎች በመንፈስ ቅዱስ ነጂነት ነው የተጻፈው። ሐዋሪያው ጴጥሮስ እንዳስተማረን “በመጽሐፍ ያለውን ትንቢት ሁሉ ማንም ለገዛ ራሱ ሊተረጉም አልተፈቀደም፤ ትንቢት ከቶ በሰው ፈቃድ አልመጣምና፥ ዳሩ ግን በእግዚአብሔር ተልከው ቅዱሳን ሰዎች በመንፈስ ቅዱስ ተነድተው ተናገሩ” (2ጴጥ. 1:20-21) ። ክፍሉ የሚናገረው ስለ መጽሐፍ ቅዱስ ነው። የእግዚአብሔር ቃል ደራሲ (ቃሉን ወደ እኛ) ያመጣው መንፈስ ቅዱስ ነው። ስለዚህ ይህንንም ቃል ሊተረጉምልንና ሊያስተምረን የሚችለው መንፈስ ቅዱስ ነው። መቼም አንድ እውነት አለ፡ ጽሑፍ ሁሉ የሚገልጸው በደራሲው ውስጥ ያለውን ሃሳብ ነው። ሲተረጎምም እንዲሁ በደራሲው ውስጥ ያለውን ሃሳብ ከማግኘት አንጻር ነው መተርጎም ያለበት። በአለም ስርዓት ያሉ ሕጎች እንኳ ሲተረጎሙ የህግ አውጪው ሃሳብ ምንድን ነው ተብሎ ይጠየቃል። ሕጉም ያንን ሃሳብ በሚያጸና መልኩ ይተረጎማል። የግዚአብሔር ቃል ደግሞ የሚገልጽልን በእግዚአብሔር ልብ ውስጥ ያለውን ሃሳብ ነው። ይህንን ሃሳብ ደግሞ ያለ መንፈስ ቅዱስ እገዛ ልንረዳው አንችልም። ስለዚህ ነው ቃሉ ይህንኑ ሲገልጽልን “መንፈስም የእግዚአብሔርን ጥልቅ ነገር ስንኳ ሳይቀር ሁሉን ይመረምራልና ለእኛ እግዚአብሔር በመንፈሱ በኩል ገለጠው። በእርሱ ውስጥ ካለው ከሰው መንፈስ በቀር ለሰው ያለውን የሚያውቅ ሰው ማን ነው? እንዲሁም ደግሞ ከእግዚአብሔር መንፈስ በቀር ለእግዚአብሔር ያለውን ማንም አያውቅም። እኛ ግን ከእግዚአብሔር እንዲያው የተሰጠንን እናውቅ ዘንድ ከእግዚአብሔር የሆነውን መንፈስ እንጂ የዓለምን መንፈስ አልተቀበልንም” (1ቆሮ. 2:10-12) በማለት ያስተምረናል። መንፈስ ቅዱስ በእግዚአብሔር ልብ ውስጥ ያለውን ሃሳብ ያውቃል። ስለዚህም ቃሉን በመግለጽና በማስተማር ወደ እውነት ሁሉ ይመራናል (ዮሐ. 16:13)።

ወገኖቼ፦ እግዚአብሔር የሚገለጠው በቃሉ ውስጥ ነው። የእግዚአብሔርን ቃል ደግሞ የሚገልጥልንና የሚያስተምረን መንፈስ ቅዱስ ነው። እግዚአብሔርን ለማወቅ ቃሉን እንወቅ፤ ቃሉን ደግሞ ለማወቅ ወደ መንፈስ ቅዱስ እንቅረብ። የቃሉን ፍቺ ያበራልናል።


Recent Posts
Archive
Search By Tags
No tags yet.
Follow Us
  • Facebook Basic Square
  • Twitter Basic Square
  • Google+ Basic Square
bottom of page